የሀገር ውስጥ ዜና

ከ245 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

By Amele Demsew

October 24, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጥቅምት 2 እስከ 8 ቀን 2016 ዓ.ም በተደረገ ክትትል ከ245 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የጉሙሩክ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ 170 ሚሊየን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 75 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የወጭ በድምሩ 245 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መያዛቸውን አስታውቋል፡፡

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ ዕጾች፣የምግብ ዘይት እና የተለያየ ሀገር ገንዘቦች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ኮንትሮባንዱን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 21 ተጠርጣሪዎችና 14 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!