Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ብናልፍ አንዱአለም በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱአለም በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር እና የአፍሪካ ህብረት ቋሚ ተወካይ ከሆኑት በረክ ባራን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ያለው የሰላም ግንባታ ሂደት ስለሚጠናከርበት ሁኔታ እና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የነበሩ የቀድሞ ታጣቂዎች ትጥቅ ፈተው በሰላም ከህብረተሰቡ ጋር መቀላቀል የሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

በተጨማሪም÷ የብሔራዊ የምክክር ሂደቱ ውጤታማ የሚሆኑበት መንገድ ላይ መወያየታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version