አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ እንደ ፀረ-ሚሳዔል እና ራዳር የምትጠቀምበትን በርካታ ሥርዓቶች ያሉት “ታድ” የተሠኘ የጦር መሣሪያ ወደ እስራዔል ማሥጠጋቷን ፔንታጎን አስታውቋል፡፡
የጦር መሣሪያዎቹን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የተለያዩ አካባቢዎች ማስጠጋት ያስፈለገው በሥፍራው የሚገኘውን ወታደራዊ ኃይላችንን ጥበቃ ለማጠናከር ነው ሲሉ የአሜሪካው መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም እስከ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት በመወንጨፍ ከሌላ አቅጣጫ የተተኮሰ ሚሳኤልን በዓየር ላይ የመምታት ዐቅም ያላቸው መሣሪያዎቹ የት አካባቢ እንደተጠመዱ ያሉት ነገር የለም፡፡
“ታድ” የተሠኙት እነዚህ የጦር መሣሪያዎች ከሌላ ወገን የሚላኩ ድሮኖችንም ሆነ ተዋጊ ጀቶችን በተገጠመላቸው ራዳር ለመለየት እና ለመምታት የሚያስችል ሥርዓት እንደተገጠመላቸው ተመላክቷል፡፡
የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል አባላትም ለግዳጅ ዝግጁ እንዲሆኑ ሚኒስትሩ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ሲል አር ቲ ዘግቧል፡፡
ከ30 ሀገራት በላይ በተሳተፉበት የትናንቱ የግብፅ የሠላም ጉባዔ እስራዔልና አሜሪካ ሳይገኙ መቅረታቸው ይታወሳል፡፡