ዓለምአቀፋዊ ዜና

ቱርክ ለቀጣናዊ ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ መፈለጓን እንደምትቀጥል ኤርዶሃን ገለጹ

By Meseret Awoke

October 21, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶሃን የእስራኤል-ሃማስን ጦርነት ጨምሮ ሀገራቸው ለቀጣናዊ ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ መፈለጓን እንደምትቀጥል አመለከቱ።

ከዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር የስልክ ውይይት ያደረጉት ኤርዶሃን ለሩሲያ-ዩክሬንም ሆነ ለእስራኤል-ፍልስጤም እንዲሁም ለሰብዓዊ ቀውስ ቱርክ መፍትሄ የምታፈላልገው ሰላማዊ መንገድን በመከተል እንደሆነ መናገራቸውን የሀገሪቱ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በኤክስ ባወጣው መረጃ ገልጿል።

ሰላማዊ መንገድን በመከተል ግጭትን ማቆም እንደሚቻል የምታምነው ቱርክ ሰላምን ለማረጋገጥ የምትችለውን ጥረት ሁሉ እንደምታደርግ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንት ኤርዶሃን ከዩክሬን ፕሬዚዳንት በተጨማሪ ከሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን (ኔቶ) ዋና ጸሐፊ ጄን ስቶልተንበርግ እና ከኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ቲአርቲ ወርልድ ዘግቧል።

#Turkey #Israel #Palestine

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!