Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ካናዳ 41 ዲፕሎማቶቿን ከሕንድ አስወጣች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕንድ በአሸባሪነት የፈረጀችው እና የካናዳ ዜግነት ያለው የሲክ ቡድን መሪ በካናዳ መገደሉን ተከትሎ በተፈጠረ አለመግባባት ካናዳ 41 ዲፕሎማቶቿን ከሕንድ አስወጥታለች።

የሕንድ ጥምር ዜግነት ካለው የቡድኑ መሪ መገደል ጀርባ የሕንድ እጅ አለበት ስትል ካናዳ ትከሳለች፡፡

በፈረንጆቹ ሰኔ 18 ቀን 2023 የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ ሕንድ በመወንጀሏ ቁጣዋን መግለጿን ተከትሎ የሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት መካረር ውስጥ ገብቷል።

ህንድም በደርዘን የሚቆጠሩ የካናዳ ዲፕሎማቶች በአስቸኳይ ሀገሯን ለቀው እንዲወጡም ጠይቃለች፡፡

ይህ የማይሆን ከሆነ ግን በሕንድ ያላቸውን የሕግ ከለላ እንደሚገፈፍ ከሁለት ሣምንታት በፊት ማስጠንቀቋን ቢቢሲ አስታውሷል፡፡

የካናዳ ባለሥልጣናት የሕንድን ማስጠንቀቂያ የ”ዓለም አቀፉን ሕግ የሚጥስ” ሲሉ ኮንነውታል፡፡

ሕንድም በበኩሏ የካናዳን ክስ መሠረተ ቢስ ስትል ነው ያጣጣለችው፡፡

ለሁለቱ ሀገሮች መካረር መንስኤ የሆነው የሲክ መሪው ሃርዲፕ በፈረንጆቹ 1997 ላይ በወጣትነት ዕድሜው ወደ ካናዳ አቅንቶ በቧንቧ ሠራተኛነት ሲተዳደር ነበር ተብሏል፡፡

ሕንድ ግለሰቡን ቀደም ሲል ከካሊስታን ታይገር ፎርስ የአሸባሪዎች ቡድን ጀርባ ሆኖ የሚያቀነባብር ዋናው ሰው ነው በሚል መወንጀሏንም ዘገባው አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version