የሀገር ውስጥ ዜና

የቤተ-መንግሥት አስተዳደር ከ38 ዓመታት በላይ ላገለገሉ ሠራተኞች እውቅና ሰጠ

By Meseret Awoke

October 19, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የቤተ-መንግሥት አስተዳደር በተለያዩ የሃላፊነት ደረጃዎች ከ38 ዓመታት በላይ ላገለገሉ ሠራተኞቹ እውቅና ሰጥቷል።

እውቅና እና የገንዘብ ስጦታ የተበረከተላቸው ሠራኞች እውቀታቸውንና ጉልበታቸውን ሳይቆጥቡና ሳይሰስቱ ሀገራቸውን ለ38 ዓመታት በቅንነት ማገልገላቸው ተገልጿል፡፡

በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የቤተ-መንግሥት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ምትኩ ዴሬሳ ÷ ሰራተኞች ሀገራቸውን በመውደድ እና በማፍቀር በታማኝነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!