Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኪም ጆንግ ኡን ከሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር መምከራቸው ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ኮሪያ ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሠርጌይ ላቭሮቭ ጋር በፒዮንግያንግ ተገናኝተው መምከራቸው ተገለጸ፡፡

ሁለቱን ወገኖች ተገናኝተው መምከራቸውን ይፋ ያደረገው የሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች አገልግሎት ነው፡፡

አገልግሎቱ በሁለቱ መካከል ስለተካሄደው ውይይት ጭብጥ ያለው ነገር እንደሌለ ላ ፕሬንሳ ላቲና አስነብቧል፡፡

ሠርጌይ ላቭሮቭ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር ዛሬ ከመገናኘታቸው በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ÷ የሁለቱ ሀገር መንግሥታት በቀጣዩ ወር በከርሰ-ምድር ማዕድናት ፍለጋ እና በኃይል አቅርቦት ጉዳይ ላይ በትብብር ለመሥራት በሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ ለመምከር እንደሚገናኙ ጠቁመዋል፡፡

በቀጣዩ ወር 10ኛው የምጣኔ ሐብት፣ ንግድ እና ሣይንሳዊ የቴክኒክ ትብብሮች ጉባዔ እንደሚያካሂዱም ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version