የሀገር ውስጥ ዜና

አመራሩ ሕዝቡን አስተባብሮ የእርሻ ቦታዎችን በማልማት የኑሮ ውድነትን ማቃለል እንደሚገባው ተገለጸ

By Amele Demsew

October 18, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በየአካባቢው ያለው አመራር ሕዝቡን አስተባብሮ የእርሻ ቦታዎችን በማልማት የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነትን ማቃለል ይገባዋል ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ፡፡

አቶ አደም በአርባምንጭ ከተማ የሚገኙ የትምህርት ተቋማትን እና በጋሞ ልማት ማኅበር እየተሠራ የሚገኘውን የእርሻ ልማት ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸው ወቅትም÷ ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ብልፅግናን ማረጋገጥ የሚያስችል ሀብት አላት ብለዋል፡፡

በየደረጃው ያለው አመራር በቁርጠኝነት ከሠራ እና ሕዝቡም አስፈላጊውን ድጋፍ ካደረገ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ማለታቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

ትምህር ላይ መሰረታዊ ለውጥ እንዲመጣ ጥራት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባም ነው ያመላከቱት፡፡

በጋሞ ልማት ማኅበር እየለማ የሚገኘው የእርሻ ሥራ የሚበረታታ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡