አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝቡን ኑሮ ለማሻሻል ዘላቂነት ያለው ጠንካራ ሥርዓት እንገነባለን ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ተናገሩ፡፡
አቶ አደም ፋራህ በአርባምንጭ ማዕከል ከ’ዕዳ ወደ ምንዳ’ በሚል መሪ ሐሳብ እየተሰጠ በሚገኘው የአመራር ሥልጠና መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የሕዝቡን ኑሮ ለማሻሻልና ማሻሻያውም ቀጣይነትና ዘላቂነት እንዲኖረው የሚያስችል ጠንካራ ሥርዓት እንገነባለን ብለዋል።
ብልጽግና ፓርቲ÷ ያሉንን ሀብቶች በአግባቡ በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚያስችል የተስተካከለ ዕይታ፣ የደረጀ እና የሐሳብ ፓርቲ ነው ብለዋል በንግግራቸው፡፡
ብልጽግናም ሆነ ሕዝቡ ከአመራሩ ብዙ እንደሚጠብቁ ያስገነዘቡት አቶ አደም÷ አመራሮች ከስልጠና የሚያገኙትን ግብዓት ወስደው በየአካባቢያቸው ያሉ መልካም አፈፃፀሞች ተጠብቀው እንዲሰፉ መትጋት ይገባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ልማቱን ለማፋጠን የሚስችል አቅም አመራሩ ከስልጠናው እንደሚያገኝ ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አመራሩ ለተሻለ ተልዕኮ ራሱን ሊያዘጋጅ ይገባል ማለታቸውን ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!