አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በአባል ሀገራቱ መካከል ያለውን የሥደተኞች ጥበቃ በተመለከተ ባዘጋጀው አዲስ የፖሊሲ ማዕቀፍ ላይ በአዲስ አበባ የማጠቃለያ ውይይት እያካሄደ ነው።
በመድረኩ የአባል ሀገራቱ ተወካዮች፣ የተባበሩት መንግስታት የሥደተኞች ኮሚሽን ተወካዮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው፡፡
በአባል ሀገራቱ መካከል የሥደተኞች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ በመድረኩ ተመላክቷል።
በዚህም በፖሊሲ የተደገፈ አዲስ የመፍትሄ አቅጣጫ የሚያሥፈልግ መሆኑ ታምኖበታል።
በመሆኑም አዲስ የሥደተኞች ጥበቃ የፖሊሲ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ለሦስት ቀናት ውይይት ሲደረግበት ቆይቷል።
ለፖሊሲው ትግበራም አባል ሀገራቱ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
በኢጋድ አባል ሀገራት ውስጥ ከ5 ሚሊየን በላይ ሥደተኞች እንደሚገኙ መጠቆሙን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!