አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራዔልን ያካተተው የግብፅ እና የአሜሪካ ውይይት ጦርነቱ በደቡብ ጋዛ ለጊዜው እንዲቆም ሥምምነት ላይ በመድረስ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡
ስምምነቱ በጋዛ እና በግብፅ መካከል ያለውን የራፋኅ ድንበር ለመክፈት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል መባሉን ዘ ግሎብ ኤንድ ሜይል ዘግቧል፡፡
እስራዔልን በማዕከላዊነት ያሳተፈው የሀገራቱ ውይይት ጦርነቱ ለበርካታ ሠዓታት እንዲቆም ሥምምነት ላይ ቢያደርስም ለምን ያኅል ሠዓት እንደሆነ ግን ቁርጥ ያለ ጊዜ አላስቀመጠም፡፡
ሦስቱ ሀገራት የራፋኅ ድንበር በኢትዮጵያ ሠዓት አቆጣጠር እስከ ምሽቱ 5 ሠዓት ክፍት እንዲሆን ተሥማምተዋል፡፡
እስካሁን ባለው መረጃ በጉዳዩ ላይ የእስራዔል ወታደራዊ ኃይል እና በእስራዔል የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ምንም አላሉም፡፡
እንዲሁም ከጋዛ በኩል የተሰማ ነገር እንደሌለ ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
በመወዳጀት ይከታተሉን፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!