አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሰሞኑን በፈረንጆቹ ጥቅምት 17 እና 18 በሚካሄደው የ ”ቤልት ኤንድ ሮድ መድረክ” ለመሳተፍ ወደ ቤጂንግ እንደሚያቀኑ ተሰምቷል፡፡
ከመድረኩ ጎን ለጎንም ፕሬዚዳንት ፑቲን ከቻይናው አቻቸው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ተጠቁሟል፡፡
በምክክራቸውም÷ የሩሲያና ቻይናን “ገደብ የለሽ” ወዳጅነት በይበልጥ ለማጠናከር እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡
ቻይና እና ሩሲያ “ገደብ የለሽ” ወዳጅነታቸውን ያወጁት ፕሬዚዳንት ፑቲን ቻይናን በጎበኙበት ወቅት በፈረንጆቹ የካቲት 2022 መሆኑ ይታወሳል፡፡
ሁለቱ ሀገራት ግዙፍ ስትራቴጂያዊ ተወዳዳሪዎቿ መሆናቸውን አሜሪካ እንደምታምን ጠቅሶ ሬውተርስ ዘግቧል፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!