Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ነፍሰ-ጡር ሴት ተኩሶ የገደለ የናይጄሪያ ፖሊስ የሞት ፍርድ ተፈረደበት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አንድ የናይጄሪያ ፖሊስ የሕግ ባለሙያ የሆነች ነፍሰ-ጡር ተኩሶ በመግደሉ የሞት ፍርድ ተፈረደበት፡፡

የናይጄሪያ ሌጎስ ከፍተኛ ፍ/ቤት ድራምቢ ቫንዲ የተባለው የናይጄሪያ ፖሊስ ላይ የሞት ፍርድ የበየነው ኦሞቦላንሌ ራሂም የተባለችውን የኅግ ባለሙያ ተኩሶ በመግደሉ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ፖሊሱ ነፍሰ-ጡሯን የኅግ ባለሙያ ተኩሶ የገደለው ከቤተሰቦቿ ጋር የገና በዓል አገልግሎት ተካፍላ ወደ ቤቷ በመመለስ ላይ ሳለች መሆኑን ግሎባል ቮይስስ የተባለው ገፅ ጨምሮ አስነብቧል፡፡

ወንጀሉን ከተፈጸመ በኋላም በአካባቢው አብረውት ከነበሩ ሌሎች የሥራ ባልደረቦቹ ጋር ከአካባቢው መሰወሩ ተነግሯል፡፡

ራሂም ላይ የተፈጸመው የግድያ ወንጀል ከዚህ ቀደም በርካታ የናይጄሪያ ፖሊሶች አሰቃቂ ወንጀል እየፈጸሙ ነው የሚለውን የዜጎች ውንጀላ ዕውነታነት ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነው ተብሎለታል፡፡

ከአሁኑ የግድያ ወንጀል ሦስት ሣምንታት ቀደም ብሎም ጋፋሩ ቡራኢሞህ የሚባል አንድ የ31 ዓመት ሰው በተመሳሳይ አካባቢ ባለ በፖሊስ የግድያ ወንጀል እንደተፈጸመበት ተገልጿል፡፡

በዘርፉ የተሠራ አንድ ጥናት እንዳመላከተው ባለፈው ዓመት ብቻ 91 ናይጄሪያውያን በተመሳሳይ ሁኔታ በፖሊሶች ግድያ ተፈጽሞባቸዋል፡፡

ራሂም ላይ የተፈጸመውን የግድያ ወንጀል አምነስቲ ኢንተርናሽናል በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ ኮንኖታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version