አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ኮን 2023 17ኛው ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን አውደርዕይ በአዲስ አበባ ተከፈተ።
አውደርዕዩ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 4 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ክፍት ሆኖ ይቆያል ተብሏል።
በአውደርዕዩ በኮንስትራክሽን ስራ ላይ የተሰማሩ የተለያዩ ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን ለማስተዋወቅ ተገኝተዋል።
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ወንድሙ ሴታ (ኢ/ር)÷ የኮንስትራክሽን ዘርፉን ለመደገፍ ዘርፈ ብዙ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረው ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የኮንስትራክሽን ዘርፉን ግብዓቶች 80 በመቶ በሀገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን እየተሰራ እንደሚገኝም ሚኒስትር ዴኤታው በመድረኩ አንስተዋል።
በአሸናፊ ሽብሩ