የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ከዓለምአቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

By ዮሐንስ ደርበው

October 11, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኤሚ ኢ ፖፕ ጋር ተወያዩ፡፡

ኤሚ ኢ. ፖፕ የመጀመርያ የሥራ ጉብኝታቸውን በኢትዮጵያ አድርገዋል፡፡

ከጉብኝታቸው ከፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ጋር ባደረጉት ውይይት÷ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ መሆኗ ከድርጅታቸው ዓላማ አንጻር ለላቀ ትብብር ቁልፍ ሚና የምትጫወት ሀገር መሆኗን አንስተዋል፡፡

በተፈናቃዮች ላይ የበለጠ መስራት እንደሚገባ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ጠይቀዋል፡፡

ፍልሰትን በተመለከተ በአካባቢው የሚመለከታቸው ሀገራት ሚኒስትሮች ስብሰባን ለማስተናገድ እየተሠራ መሆኑንም እንዳመለከቱ የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት መረጃ ገልጿል።