Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አካላዊ ጥንካሬያቸውን ለማሳየት ሰባት መኪኖችን ያነባበረው ኩባንያ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው የመኪና አምራች ኩባንያ ቼሪ አዲስ ያመረታቸውን የኤሌክትሪክ መኪኖች ከአሉሚኒየም የተሰራው አካላቸው ምን ያክል ጠንካራ እንደሆነ ለማሳየት ሰባት መኪኖችን ወደላይ በማነባበር የማስተዋወቅ ዘዴ ይዞ መጥቷል፡፡

በቻይና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ምርት በአሁኑ ጊዜ በሰፊው እየተከናወነ ሲሆን፤ አምራቾች ፉክክሩን በበላይነት ለመምራት ሁሉንም ዓይነት የማስታወቂያ ስልቶችን እየተጠቀሙ ነው፡፡

የቻይና ኩባንያ ቼሪ በጥራቱ፣ በዋጋው፣ በማራኪ ዲዛይኑ እና በባትሪው ቆይታ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘውን አዲሱን ኢ ኪው-7 የኤሌክትሪክ መኪና ይውሰዱ እያለ ሲያስተዋውቅ ተስተውሏል።

ኩባንያው አዲሱ ኢ ኪው-7 መኪና ባትሪው አንዴ ከተሞላ ከ412 እስከ 512 ኪሎ ሜትር መጓዝ እንደሚችል ተነግሮለታል።

ይህ መገለጫ የመኪና ምርቶቹን ከሌሎች ተፎካካሪዎች ሊለዩት እንደማይችሉ የተገነዘበው ኩባንያው፤ ጎልቶ እንዲታይ የመኪና ህንፃ በመፍጠር በአልሙኒየም አካል ጥንካሬ ላይ ለማተኮር ወስኗል፡፡

የሀይዌይ ደህንነት ኢንሹራንስ ኢንስቲትዩት እንዳስቀመጠው ከፍተኛውን የደህንነት ደረጃ ለማግኘት አንድ ተሽከርካሪ የራሱን ክብደት 4 እጥፍ መሸከም መቻል አለበት።

ቼሪ ግን ያ በቂ እንዳልሆነ በመወሰን ሰባት ተሽከርካሪዎችን በማነባበር ከታች ያለው ተሽከርካሪ በላዩ ላይ የተቀመጡ ስድስት መኪኖችን የመሸከም አቅም እንዳለው ማሳየቱን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።

Exit mobile version