Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የመጀመሪያው የኢትዮ-ቺሊ የፖለቲካ ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እና የቺሊ የፖለቲካ ምክክር ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሄደ።

ምክክሩን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ እና አሜሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እስክንድር ይርጋ እና በቺሊ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ እና የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሁዋን ፒኖ መርተውታል።

በመክፈቻው ወቅት በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ውይይት መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ሀገራቱ በፈረንጆቹ 2022 በተፈራረሙት የፖለቲካ ምክክር የመግባቢያ ሰነድ ላይ መነሻውን ያደረገው ምክክሩ፥ ዓለም አቀፍ መድረኮችን ጨምሮ ሀገራቱ በተለያዩ የትብብር ዘርፎች ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማስፋት ያለመ ነው ተብሏል።

ኢትዮጵያ ከቺሊ ጋር ላላት ግንኙነት ከፍ ያለ ቦታ እንደምትሠጠው እስክንድር ይርጋ በውይይቱ ወቅት ገልጸዋል፡፡

አምባሳደር ሁዋን በበኩላቸው÷ በኢኮኖሚና በትምህርት ዘርፍ እንዲሁም በባለብዙ ወገን መድረኮች ያለውን ግንኙነት ማጠናከር እንደሚገባ አመልክተዋል።

የምክክር መድረኩ የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነቶች በመገምገምና በተለያዩ አኅጉራዊ እና የባለ-ብዙ ወገን የጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር መሥራት ሚቻልባቸውን ሁኔታዎችን የቃኘ ነበር።

ሁለቱ ወገኖች የሁለትዮሽ ትብብራቸውን እና የቆየ ግንኙነትታቸውን ለማሳደግ ቃል ገብተው ውይይታቸውን አጠናቀዋል።

ኢትዮጵያና ቺሊ መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት በፈረንጆቹ 1965 ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version