የሀገር ውስጥ ዜና

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀረቡለትን እቅዶች መርምሮ አጸደቀ

By Shambel Mihret

October 10, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ያካሄደው የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀረቡለትን እቅዶች መርምሮ አጽድቋል፡፡

በጉባዔውም የሕገመንግሥት ትርጉምና ውሳኔ አፈጻፀም ክትትል ቋሚ ኮሚቴ፣ የመንግስታት ግንኙነት የዲሞክራሲ አንድነትና የሕገመንግሥት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ፣ የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ፣ የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴና የሕገ መንግሥትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ያቀረቡት የ2016 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ተወያይቶ አጽድቋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት የቀረቡላቸውን እቅዶች ካደመጡ በኋላ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ያቀረቡ ሲሆን÷ የየቋሚ ኮሚቴዎቹ አመራሮችም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር እና ሌሎች የሥራ ሀላፊዎች በጉባዔው መገኘታቸውንም የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡