ቢዝነስ

ሀገር አቀፍ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ኢንቨስትመንት ዐውደ-ርዕይ ነገ ይከፈታል

By ዮሐንስ ደርበው

October 09, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ሣይንስ ሙዝየም ለአንድ ወር የሚቆይ ሀገር አቀፍ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ኢንቨስትመንት ዐውደ-ርዕይ ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ክፍት በሚሆነው ዐውደ-ርዕይ÷ በሁሉም ክልሎች ያሉ የቱሪዝም መዳረሻዎች፣ ባሕላዊ አልባሳት፣ ቁሶች፣ ኢትዮጵያን የሚያስተዋውቁ ባሕልና እሴቶች ይቀርባሉ ተብሏል፡፡

የቱሪዝም ዘርፉ ላይ ያኮሩ የፓናል ውይይቶች እንደሚካሄዱም ነው በሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ዓለማየሁ ጌታቸው ለኢዜአ የተናገሩት፡፡

ከ100 በላይ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ አካላት በዐውደ-ርዕዩ እንደሚሳተፉ አስረድተዋል፡፡

ዐውደ-ርዕዩን የውጭና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች፣ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ተማሪዎችና የተለያዩ የማሕበረሰብ ክፍሎች ይጎብኙታል ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል፡፡

ሀገሪቱ ያላትን የተፈጥሮ ሃብትና ሌሎች ፀጋዎች ከማስተዋወቅ ባለፈ ዘርፉን በተሻለ መልኩ ለማሳደግ ዐውደ-ርዕዩ የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም አመላክተዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!