የሀገር ውስጥ ዜና

ዜጎችን በሕጋዊ መንገድ ለሥራ ወደ ውጪ እንዲጓዙ የሚደግፍ የቴክኒክ ቡድን ተቋቋመ

By Alemayehu Geremew

October 09, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሥራ ወደ ውጪ የሚጓዙ ዜጎችን በሕጋዊ መንገድ እንዲጓዙና በመዳረሻ ሀገራት ችግር እንዳይገጥማቸው የሚያግዝ የቴክኒክ ቡድን ተቋቋመ።

ቡድኑ የተመሠረተው የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር መሆኑ ተገልጿል።

የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት ጋር በመተባበር በጋራ በሰጡት መግለጫ ÷ የቴክኒክ ቡድኑ ÷ ዜጎች ለሥራ ከሀገር ሲወጡ በሕጋዊ መንገድ እንዲወጡ የሚያግዝ መሆኑን አስረድተዋል።

በተጨማሪም ለሥራ ወደ ውጪ የሚጓዙ ዜጎች አሥፈላጊ ሥልጠናዎችን እንዲያገኙና ስለሚጓዙበት ሀገርም በቂ መረጃ ኖሯቸው የሚገባቸውን ክፍያ እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ተብሏል።

ቴክኒካል ቡድኑ ለሥራ ከሀገር የሚወጡ ዜጎችን የሚገጥሟቸውን ችግሮች ይፈታል የሚል ተሥፋም ተጥሎበታል።

በፍቅርተ ከበደ