የሀገር ውስጥ ዜና

ዶ/ር ሊያ ታደሰ ከዓለም አቀፍ የክትባት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

By ዮሐንስ ደርበው

October 07, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ከዓለም አቀፍ የክትባት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጂሮም ኪም (ፕ/ር) ጋር ተወያተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ ዓለም አቀፉ የክትባት ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን እና አርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በክሊኒካል ሙከራዎች እና በሀገር ውስጥ ክትባት የማምረት አቅምን ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል፡፡

እንዲሁም በአፍሪካ የክትባት ኅብረት ዙሪያ በጋራ ለመስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ዶ/ር ሊያ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል፡፡