Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካቢኔ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

በዚሁ መሠረት ካቢኔው ባካሄደው ውይይት÷ በአሶሳ ከተማ በሚገነባው ዘመናዊ ሙዚየም እንዲሁም በበተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) ለሚገነባው ቢሮ ከይዞታቸው ለሚነሱ ግለሰቦች የካሳ ጥያቄ ላይ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

እንዲሁም ክልሉ ከሚታወቅባቸው የተፈጥሮ ሀብቶች አንዱ በሆነው የ “ቀርቀሃ/ሽመል/ ልማት ጥበቃና አጠቃቀም መመሪያ” ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን የቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም ካቢኔው በክልሉ ለሌማት ቱርፋት ትግበራ የሚውል የእንስሳት ግዥን በተመለከተ በመወያየት ውሳኔዎችን በማሳለፍ የስራ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version