Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአይ ኦ ኤም ዳይሬክተር ጀነራል በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ዓቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) ዳይሬክተር ጀነራል ኤሚ ኢ ፖፕ በሚቀጥለው ሳምንት በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ።

 

ዳይሬክተር ጀነራሏ በኢትዮጵያ የሚኖራቸውን የስራ ጉብኝት አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

 

ጉብኝታቸው ኢትዮጵያ ስደተኞችን በመቀበልና በማስተናገድ እንዲሁም ተዛማጅ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ረገድ ያላትን ዓለም አቀፋዊ ሚና የሚያጎላ እንደሆነም ተጠቁሟል።

 

በአይ ኦ ኤም የ72 ዓመታት ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያዋ ሴት ዳይሬክተር ጀነራል የሆኑት ኤሚ ኢ ፖፕ የመጀመሪያ የስራ ጉብኝታቸውን በኢትዮጵያ እንደሚጀምሩ ተገልጿል።

Exit mobile version