Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሶማሊያ ጦርና የአካባቢ ሚሊሻዎች በትንሹ 100 የአልሸባብ አሸባሪዎችን መደምሰሳቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያ ጦርና የአካባቢ ሚሊሻዎች በማዕከላዊ ጋልሙድ ግዛት በትንሹ 100 የአልሸባብ አሸባሪዎችን መደምሰሳቸውን የሀገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ዳውድ አዌይስ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፤ ጦርነቱ በተካሄደባቸው ዊሲል እና ሻቤሎው ወረዳዎች አካባቢ በአሸባሪዎቹ ላይ እርምጃ ተወስዷል።

መከላከያ ሰራዊቱ እና ሚሊሻዎቹ ከ100 በላይ አሸባሪዎችን ማቁሰላቸውንም ገልፀዋል።

የሀገሪቱ ጦር እና ዓለም አቀፍ የጸጥታ አጋሮች የአሸባሪዎች እና አዛዦች ቡድን በጦር ኃይሉ ተከቦ ባለበት በመካከለኛው ሸበሌ ክልል ከመሃዳይ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን አዌይስ ተናግረዋል።

ይህ የተነገረው በደቡብ ማዕከላዊ ክልሎች በተካሄደ የተለየ ወታደራዊ ዘመቻ ሶማሊያ በሁለት ወራት ውስጥ 1 ሺህ 650 የአልሸባብ አሸባሪዎችን መደምሰሷንና ከ550 በላይ ማቁሰሏን ከገለፀች ከአንድ ቀን በኋላ ነው።

ሶማሊያ በዋናነነት ስጋት በሆኑት በአልሸባብ እና አይ ኤስ አሸባሪ ቡድኖች ለዓመታት የጸጥታ ችግር ስትታመስ መቆየቷን አናዶሉ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version