Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በዘንድሮ የመስኖ ልማት 3 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ ለማልማት ታቅዷል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮ የመስኖ ልማት 3 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ ለማልማት ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በጅማ ከተማ ሀገራዊ የመስኖ ስንዴ ልማት ንቅናቄ መድረክ በማካሄድ ላይ ነው።

በመድረኩ የተገኙት የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) እንዳሉት÷ በዚህ አመት ሶስት ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ በመስኖ ለማልማት ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል።

ይህም ባለፈው ዓመት በበጋ መስኖ ከለማው 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር መሬት በ1 ነጥብ 7 ሚሊየን ሄክታር መሬት ብለጫ እንዳለው ገልፀዋል።

በተጨማሪም በመኸርና በክረምት እርሻ የአፈር ማዳበርያ እጥረት እንዳይፈጠር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

ለዘንድሮ የበጋ መስኖ ከነባር የውሃ ፓምፖች በተጨማሪ 12 ሺህ የውሃ ሞተር ፓምፖች ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸው ተገልጿል።

Exit mobile version