የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ ክልል በ80 ሚሊየን ብር ወጪ በጉራጌ ዞን ያስገነባውን ትምህርት ቤት አስመረቀ

By Amele Demsew

October 05, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል በ80 ሚሊየን ብር ወጪ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ያስገነባውን የጉስባጃይ ኢፋ ቦሩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን አስመርቋል፡፡

ትምህርት ቤቱ 8 ብሎኮች እና 46 ክፍሎች ያሉት ሲሆን በ80 ሚሊየን ብር ወጪ ተገንብቶ ለምረቃ መብቃቱ ተገልጿል፡፡

ለትምህርት ቤቱ ግንባታ ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ.ም የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ግንባታው ተጠናቆ ከ250 በላይ ተማሪዎች እየተማሩበት ይገኛል።

በፍቅርተ ከበደ