የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላት ጋር መከሩ

By Meseret Awoke

October 03, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ በ2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላት ጋር ተወያዩ፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ ጠዋት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የሥራ ሂደቱን በተመለከተ ውይይት መደረጉ ተግልጿል።

በስብሰባው የተቋማት ግንባታ፣ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ፣ የውይይት ሂደት መቅረጽ፣ የውይይት ተሳታፊዎችን መለየት እንዲሁም ቀጣይ የሚሠሩ ተግባራትንና ለተሳካ የውይይት ሂደት መቀረፍ ያለባቸውን ችግሮች ጨምሮ ኮሚሽኑ እስካሁን ያከናወናቸውን ተግባራት ጠቅሷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ መጪው ሀገር አቀፍ ምክክር በአጨቃጫቂ ጉዳዮች ላይ መግባባትን ለማምጣት በምናደርገው የጋራ ጥረት ወሳኝ ምዕራፍ እንደሚሆን አምናለሁ ብለዋል።

አክለው ዛሬ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላትን አግኝቼ ሥራዎቻቸው ስላሉበት ደረጃ ተወያይተናል ሲሉም ገልጸዋል።