Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሪጋ የጎዳና ላይ ሩጫ ለተሳተፉ አትሌቶች የእውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በላቲቪያ ሪጋ የዓለም የጎዳና ላይ ውድድር ለተሳተፉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አባላት የእውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

በሪጋ የዓለም የጎዳና ላይ ውድድር የተሳተፉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አባላት ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ልዑካኑ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ እና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረ/ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

በቀጣይም በላቲቪያ ሪጋ በተካሄደው የዓለም የጎዳና ላይ ውድድር ለተሳተፉ አትሌቶች በስካይ ላይት ሆቴል የእውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

ኢትዮጵያ በሪጋ የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ሁለት ወርቅ፣ አራት ብር እና አንድ የነሐስ ሜዳልያ በማግኘት 2ኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡

Exit mobile version