አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግሸን ደብረ – ከርቤ ዓመታዊ የንግሥ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የደቡብ ወሎ ዞን ባሕልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ፡፡
በዓሉ በሰላም እንዲከበር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን የመምሪያው ኃላፊ መስፍን መኮንን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
አንድ ሚሊየን የሚጠጋ የሀገር ውስጥ ጎብኚም በበዓሉ ላይ መገኘቱን ነው የተናገሩት፡፡
በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ዕክል እንዲከበር አስተዋጽኦ ላበረከቱ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የበዓሉ አስተባባሪዎች እና የጸጥታ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የግሸን ደብረ – ከርቤ የንግሥ በዓል በየዓመቱ መስከረም 21 ቀን በደማቅ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ይከበራል፡፡
በሰለሞን ይታየው