የሀገር ውስጥ ዜና

የአሸባሪው አልሸባብ ቡድን ሊያደርስ የነበረው ጥቃት በመከላከያ ሠራዊቱ ከሸፈ

By Amele Demsew

October 02, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪው አልሸባብ ቡድን ሊያደርስ የነበረው ጥቃት በመከላከያ ሠራዊቱ ከሽፏል፡፡

የሽብር ቡድኑ በሱማሌ ክልል በዶሎ አዶ ወረዳ በህዝብና በሀገር ላይ ጥቃት ለመፈፀም ስድስት ጀሪካን ተቀጣጣይ ኬሚካል እና 3ሺህ የብሬን ጥይት በመያዝ በአጥፍቶ ጠፊዎች ጥቃት ሊፈፅም የነበረ ቢሆንም በግዳጅ ቀጠናው በሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት እና በወረዳው የፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል፡፡

ብረጋዴር ጀነራል ጌታቸው ሀብታሙ እንደገለፁት ÷የሽብር ቡድኑ ከዚህ ቀደምም በሀገር ላይ ውድመት እና ሽብር ለማድረስ ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ማድረጉን ገልፀው ነገር ግን በሠራዊቱና በህዝባችን የነቃ ክትትል የሽብር ቡድኑ ሃሳብ ሳይሳካ በቁጥጥር ስር እየዋለ ነው ብለዋል፡፡

መቶ አለቃ ፈንታ አየለ በበኩላቸው÷ በቀጠናው የሚገኘውን የአልሸባብ ቡድን ሆነ የውስጥ እና የውጭ ፀረ ሠላም ሀይሎችን በመመከት ደረጃ የሠራዊቱ ሞራልና ብቃት የላቀ መሆኑን መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡