የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የደንቢ ሐይቅ ሎጅ” የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ

By Shambel Mihret

October 01, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ‹‹ገበታ ለትውልድ›› ውጥን አካል የሆነውን ‘የደንቢ ሐይቅ ሎጅ’ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደቡብ ምዕራብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በጉብኝታቸው ከ1 ዓመት ተኩል በኋላ በሚድሮክ ኢትዮጵያ የሚጠናቀቀው የ‹‹ገበታ ለትውልድ›› ውጥን አካል የሆነውን ‘የደንቢ ሐይቅ ሎጅ’ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡

የሚተገበረው የልማት ስራ የአካባቢውን የተፈጥሮ ሃብት የበለጠ አጉልቶ እንደሚያወጣም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡