አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ዞን ወደ 530 ሺህ ሄክታር መሬት በቡና መሸፈኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በማሕበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው በቡና ከተሸፈነው መሬት ውስጥ 50 በመቶ የሚሆነው ባለፉት ሦስት አራት ዓመታት የተተከሉ የአረንጓዴ ዐሻራ ውጤት እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጅማ ከተማና ዙሪያዋ የሁለት ቀናት ቆይታ አድርገዋል፡፡