የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲዋና በክረምት ወራት የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ለአቅመ ደካማ ዜጎች ተላለፉ

By Melaku Gedif

October 01, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በክረምት ወራት የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ለአቅመ ደካማ ዜጎች ተላልፈዋል፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷በዛሬው ዕለት በክረምት ወራት የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ለአቅመ ደካማ ዜጎች እና ለሀገር ባለውለታዎች መተላለፋቸውን አንስተዋል፡፡

በዚህም 203 የመዲናዋ ነዋሪዎችን የቤት ባለቤት ማድረግ መቻሉን ነው የገለጹት፡፡

መኖሪያ ቤቶቹ ባለሃብቶችን፣ የግልና መንግስታዊ ተቋማትን እንዲሁም የመንግስት ሰራተኞችን በማስተባበር የተገነቡ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ከአዲስ ዓመት ወዲህም ዛሬ የተላለፉትን ጨምሮ 1 ሺህ 889 ቤቶችን ለነዋሪዎች ማስረከብ መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡

በዚህ በጎ ስራ ላይ አሻራቸውን ላኖሩ አመራሮች፣ ባለሃብቶች ፣ የመንግስት እና የግል ተቋማትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡