ስፓርት

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለቱ የማንቼስተር ከተማ ክለቦች ሲሸነፉ አርሰናል ድል ቀንቶታል

By Feven Bishaw

September 30, 2023

 

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 19 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 7ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሁለቱ የማንቼስተር ከተማ ክለቦች ተሸንፈዋል።

ከቀትር በኋላ በተካሄደ ጨዋታ አስቶንቪላ ብራይተንን 6 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

በተመሳሳይ 11 ሰአት ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ማንቼስተር ሲቲ በወልቨርሃምፕተን ወንደረርስ 2 ለ 1 እንዲሁም ሌላኛው የማንቼስተር ከተማ ክለብ ማንቼስተር ዩናይትድ በክሪስታል ፓላስ 1 ለ 0 ተሸንፈዋል።

ከሜዳው ውጭ ከበርንማውዝ የተጫወተው አርሰናል 4 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ደረጃውን ወደ 2ኛ አሻሽሏል።

ኤቨርተን በሉተን ታወን 2 ለ 1 ሲሸነፍ ኒውካስትል ዩናይትድ በርንሌይን 2 ለ 0 አሸንፏል።

በሜዳው ሼፊልድ ዩናይትድን ያስተናገደው ዌስትሃም ዩናይትድ በተመሳሳይ 2 ለ 0 አሸንፏል።

በተመሳሳይ ቶተንሃም ሊቨርፑልን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡