Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሦስት ተቋማት በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመረጃ መረብ ደኀንነት አስተዳደር፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና የአማራ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የሦስትዮሽ ስምምነት ተፈራረሙ።

 

ሥምምነቱ የመሬት ሕገ ወጥ ወረራ እና መሠል ችግሮችን ለመፍታት ወሳኝ ነው ሲሉ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ  የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተሞችና መሠረተ ልማት ቢሮ ኅላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

 

የቴክኖሎጂ ትግበራው ዕውቀትን በማስተላለፍ እና ብክነትን በማስወገድ ሚናው ከፍተኛ በመኾኑ በፍጥነት ወደ ተግባር እንደሚገባም የኢንሳ ዋና ዳይሬክተሩ  ሰለሞን ሶካ ገልጠዋል።

 

ከክልሉ ዋና ከተማ ባሕር ዳር በመጀመር ወደ ታች ለማስፋት እንደሚሠራ ማንሳታቸውን የአስተዳደሩ መረጃ ያመላክታል።

 

የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና በበኩላቸው፥ “ሀገር ከተቋማችን የምትጠብቀውን ለማበርከት እየሠራን ነው” ብለዋል።

 

አያይዘውም “ከክልሉ ጋር የተፈራረምናቸው ሥምምነቶች እንዲሳኩ ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን” ነው ያሉት።

Exit mobile version