ዓለምአቀፋዊ ዜና

የሃሪ ፖተር ፊልም ተዋናይ ማይክል ጋምቦን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

By Amele Demsew

September 28, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃሪ ፖተር ፊልም ተዋናይ ማይክል ጋምቦን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

ማይክል ጋምቦን በተወለደ በ82 ዓመቱ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ቤተሰቦቹ አስታውቀዋል፡፡

ተዋናዩ እጅግ ተወዳጅ በሆኑት የሃሪ ፖተር ተከታታይ ፊልሞች ላይ በመተወን እውቅናን አትርፏል፡፡

ማይክል ጋምቦን ባደረበት የሳምባ ምች ሕመም ሆስፒታል ውስጥ ከሰዓታት በፊት ማረፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡