Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የመስቀል ደመራ ሥነ- ሥርዓት ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል ደመራ ሥነ – ሥርዓት በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ተከብሯል፡፡

እንዲሁም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመራ ሥነ – ሥርዓት በሃይማኖታዊ ሥርዓቱ መሠረት ተከናውኗል፡፡

በሥነ – ሥርዓቱ ላይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ብጹዓን አባቶች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን፣ የእምነቱ ተከታዮች እንዲሁም ዲፕሎማቶች እና ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ጎብኚዎች ተገኝተዋል፡፡

Exit mobile version