አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ተከበረ፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብጹዓን አባቶች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን፣ የእምነቱ ተከታዮች እንዲሁም ዲፕሎማቶች እና ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ጎብኚዎች በተገኙበት ነው የደመራ በዓል የተከበረው፡፡
በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን መሪነት የደመራ በዓል ተከብሯል።
በመሳፍንት እያዩ