Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለደመራ በዓል የመስቀል አደባባይን የማፅዳት መርሐ ግብር ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደመራ በዓል የሚከበርበት የመስቀል አደባባይን የማፅዳት መርሐ ግብር ተከናውኗል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ጥራቱ በየነ በመርሐ ግብሩ ላይ እንደገለጹት÷ የዘመቻው ዋና ዓላማ ከጽዳት ባሻገር ቦታው ላይ በመገኘት በዓሉን ለሚያከብሩ ወገኖች አብሮነትን ለማሳየት ነው፡፡

በዓሉ ሃይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ አብሮነትን በሚያሳይ መልኩ እንዲከበር የመዲናዋ ነዋሪዎች የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በጽዳት ዘመቻው የተለያየ እምነት ተከታይ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የመዲናዋ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

Exit mobile version