ስፓርት

የሰሜን ለንደን ደርቢ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

By Mikias Ayele

September 24, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ለንደን ደርቢ አርሰናል ከቶተንሃም ሆትስፐር ያደርጉት ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

ቶተንሃም የጨዋታ ብልጫ በወሰደብት የሰሜን ለንደን ደርቢ አርሰናል ክርስቲያን ሮሜሮ በራሱ ላይ ባስቆጠራት ግብ መምራት ቢችልም ሰን ሁንግ ሚን ቶተንሃምን አቻ አድርጎ የመጀመሪያውን አጋማሽ አንድ አቻ አጠናቅቀዋል፡፡

ከእረፍት መልስ በድጋሚ አርሰናል በቡካዮ ሳካ የፍፁም ቅጣት ምት 2ኛ ግብ አስቆጥሮ መምራት ቢችልም ሰን ሁንግ ሚን በጅምስ ማዲሰን ታግዞ ባስቆጠራት ግብ ቶተንሃምን አቻ ማድረግ ችሏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም በጎል ክፍያ ተበላልጣው ቶተንሃም 4ኛ ደረጃን ሲይዝ÷ አርሰናል ደግሞ 5ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡

በሌላ ጨዋታ የውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ቼልሲ ኦሊ ዋትኪንስ ባስቆጠራት ግብ በአስቶን ቪላ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡

ሊቨርፑል ዌስትሃምን እንዲሁም ብራይተን ደግሞ ቦርንማውዝን በተመሳሳይ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል፡፡