የሀገር ውስጥ ዜና

የመስቀል ደመራ በዓል እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር የሕብረተሰቡ ሚና የጎላ ነው ተባለ

By Amele Demsew

September 23, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ ሰላም እንዲከበር ሕብረተሰቡ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጥሪ አቀረበ፡፡

ጉባኤው ከአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ጋር በመሆን የመስቀል የደመራ በዓልን አስመልክቶ ከአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች ጋር ምክክር አካሂዷል።

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ÷ የሃይማኖቱ ተከታዮች በዓሉን ሲያከብሩ አብሮነትን በሚያጎለብት መልኩ ሊሆን ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡