ስፓርት

ሉሲዎቹ ከቡሩንዲ አቻቸው ጋር ነጥብ ተጋሩ

By Feven Bishaw

September 22, 2023

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታው 9 ሰዓት ከብሩንዲ አቻው ጋር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም አካሂደዋል ።

በዚህም ሉሲዎቹ በመጀመሪያው አጋማሽ በረድኤት አስረሳኸኝ ጎል ተጋጣሚያቸውን 1 ለ 0 መምራት ችለው ነበር፡፡

ሆኖም በሁለተኛው አጋማሽ የብሩንዲ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በካንያሙኔዛ ኤሪካ ግብ አቻ መሆን ችለዋል፡፡

ጨዋታውም በ1 አቻ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን÷ የመልሱ ጨዋታ በመጪው ማክሰኞ አበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚደረግ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡