Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ምድርን የሚያክል ከብረት የተሰራ ፕላኔት ተገኘ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጠንካራ ብረት የተሰራ መጠኑ ምድርን የሚያክል ፕላኔት በአቅራቢያው ያለ ኮከብን እየዞረ መገኘቱ ተሰማ፡፡

ግሊሴ 367 ቢ ወይም ታሃይ የተባለው ፕላኔት ከብረት የተሰራ መሆኑ የተለየ የሚያደርገው ሲሆን፥ በ7 ነጥብ 7 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ኮከቡን እንደሚዞረው ተገልጿል።

ውስጡ ባሉ ነገሮች ከምድር በበለጠ ወይም በእጥፍ እጅግ በጣም ጥቅጥቅ ያለ ነው የተባለ ሲሆን፥ ይህም ማለት ፕላኔቱ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚቻልበት ደረጃ ስሪቱ ብረት ነው፡፡

የስነ ፈለክ ተመራማሪዎች ፕላኔቱን ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ ማግኘታቸው ቢጠቀስም፥ በአስትሮፊዚካል ጆርናል ሌተርስ ላይ የተደረገ አዲስ ጥናት የፕላኔቱ አጠቃላይ ሁኔታ በተሻሻሉ መለኪያዎች እየተጣራ መቆየቱ ተነግሯል።

አዲሱ ጥናት እንደሚያመላተው ፕላኔቱ 63 በመቶ የምድር ክብደት ያለው ሲሆን ፥ እንደ ኔፕቱን የመሰለ የጋዝ ቅሪት ሊሆን እንደሚችልና ሌሎች ግምቶች ስለአፈጣጠሩ ተሰንዝሯል፡፡

በብረት ለበሷ ፕላኔት ዙሪያ እየተደረገ ያለው ጥናት እንደቀጠለ መሆኑንም ሣይንስ አለርት ዘግቧል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version