Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሸገር ከተማ በ16 ቢሊየን ብር ወጪ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ሊገነቡ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሸገር ከተማ አስተዳደር ለገ ጣፎ ለገዳዲ ክፍለ ከተማ የተገነቡ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል።

ፕሮጀክቶቹ 374 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸው ሲሆን÷በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉ ዜጎች የተገነቡ ቤቶች፣ የቅድመ መደበኛ ት/ቤቶች፣ የገበያ ማዕከል እና የመንገድ ማስዋብ ሥራዎችን ያካተቱ ናቸው።

በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ  የሸገር ከተማ ም/ከንቲባ ጉዮ ገልገሎ እንደገለጹት÷አስተዳደሩ ከተመሰረተ ጀምሮ የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን እየገነባ ነው።

የተመረቁ ፕሮጀክቶችም የከተማውን ነዋሪዎች በትምህርት፣ በጤናና በኢኮኖሚ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በ2016 በጀት ዓመትም በ16 ቢሊየን ብር ወጪ የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ለመገንባት ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

Exit mobile version