የሀገር ውስጥ ዜና

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በ2016 ዓ.ም በነባሩ ስርዓት መደበኛ ተማሪዎችን እንደሚቀበል ገለጸ

By Amele Demsew

September 21, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ትምህርት ዘመን በነባሩ ስርዓት የመደበኛ ተማሪዎችን እንደሚቀበል አስታውቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ÷ በዩኒቨርሲቲው እየተከናወኑ የሚገኙ የማሻሻያ ስራዎችን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም÷ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ መሆኑን ተከትሎ የሽግግር ሒደት ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

የሽግግር ሒደቱ እስኪጠናቀቅ ድረስም ነባር አሰራሮች ባሉበት እንደሚቀጥሉ ነው የተናገሩት፡፡

ዩኒቨርሲቲው የሚቀይራቸው አሰራሮች ሲኖሩም በየጊዜው የማሳወቅ ስራ እንደሚከናወን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የራስ ገዝነት ሽግግር ጊዜ ከአንድ ዓመት እስከ አንድ ዓመት ተኩል እንደሚጠናቀቅም ተጠባባቂ ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡

በዘቢብ ተክላይ

#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!