አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከሁለት የስኳር ፋብሪካዎች ጋር የውል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
ስምምነቱ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ለስኳር ፋብሪካዎቹ የንብረት ትመና በማድረግ እና የፋይናንስ ድጋፍ የሚያገኙበትን የጥናት እና ምርምር ሥራ በማከናወን ወደ ተሻለ ምርታማነት ለማሸጋገር ያለመ ነው ተብሏል።
የውል ስምምነቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የትራንስፎርሜሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም ከተማ ከከሰምና ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሥራ አስኪያጆች ጋር ተፈራርመውታል፡፡
የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት በጥናት እና ማማከር ላለፉት 40 ዓመታት በላይ የተለያዩ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን እውን ማድረጉን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል።
ከዚህ ቀደም ከ3 ግዙፍ የስኳር ፋብሪካዎች እና ከሌሎችም ተቋማት እንዲሁም ፕሮጀክቶች ጋር የጥናት፣ ምርምር እና የማማከር ሥራዎችን ለማከናወን የውል ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!