Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የብሔራዊ ቡድኑ የቀድሞ ሁለት ተጫዋቾች ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ተጫዋች የነበሩት እሸቱ ገብረህይወት እና ቴዎድሮስ አስገዶም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

በ1950ዎቹ እና 60ዎቹ ተጫውተው ያሳለፉት እሸቱ ገብረህይወት በ1960 ዓ.ም በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባል ነበሩ።

ከዚህ ባለፈም በአንጋፋው ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ በተጫዋችነት አሳልፈዋል።

በተመሳሳይ በተለያዩ ክለቦች ተጫውቶ ያሳላፈው የቀድሞው ተጫዋች ቴዎድሮስ አስገዶም ባጋጠመው ህመም ምክንያት በሀገር ውስጥና በውጭ ሃገር ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ቴዎድሮስ በተለይ በ1990ዎቹ ሐረር ቢራ፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ መድን ፣ ትራንስ ኢትዮጵያ እና በሌሎች ክለቦች ተጫውቶ ያሳለፈ ተጫዋች ነበር።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሁለቱ የቀድሞ ተጫዋቾች ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን የገለፀ  ሲሆን ለቤተሰቦቻቸው ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለስፖርት ቤተሰቡ መፅናናትን ተመኝቷል።

Exit mobile version