ቢዝነስ

9 የልማት ድርጅቶች 8 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘታቸው ተነገረ

By Alemayehu Geremew

September 20, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ሥር ያሉ ዘጠኝ የልማት ድርጅቶች ከታክስ በፊት የ8 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘታቸው ተገለጸ፡፡

በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት በአስተዳደሩ ሥር ካሉት የልማት ድርጅቶች በአጠቃላይ 45 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ጠቅላላ ገቢ መገኘቱንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ገቢው ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ27 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተጠቁሟል።

ድርጅቶቹ ለተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች 604 ነጥብ 79 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን መወጣታቸውም ነው የተገለጸው፡፡

በበጀት ዓመቱ በቋሚ፣ በኮንትራትና በጊዜያዊ ቅጥር ለ65 ሺህ 371 ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውም በዘገባው ተመላክቷል።