የሀገር ውስጥ ዜና

9 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ዋጋ ያላቸው የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደረገ

By ዮሐንስ ደርበው

September 20, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል 9 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ዋጋ ያላቸው የትምህርት ቁሳቁሶች ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች እንዲውሉ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ድጋፉ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ፣ ሴቶች፣ ሕጻናት እና ወጣቶች ቢሮ፣ በክልሉ ከሚገኙ መንግስታዊና የግል ድርጅቶች እንዲሁም ከባለሃብቶች የተሰበሰበ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

ደብተር፣ እስክርቢቶና ቦርሳን ያካተተውን ድጋፍ ለወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤቶች መተላለፉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

ከ 6 ሺህ በላይ ተማሪዎችም በተደረገው ድጋፍ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!