አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው ሳምንት 125 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ኢትዮጵያውያኑ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር ነው በአየርና ባቡር ትራንስፖርት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የተደረገው፡፡
በነገው ዕለትም ተጨማሪ 95 ፍልሰተኞችን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ መሆኑን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡
የጅቡቲ-የመን መንገድ እጅግ አደገኛ እና በየቀኑ የብዙዎችን ሕይወት እየቀጠፈ የሚገኝ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ስለሆነም ዜጎች ራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ከዚህ አደጋ በመጠበቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡